የቆንስላ አገልግሎት ለማግኘት ተገልጋዮች አሟልቶ መቅረብ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
በዶሃ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ
ግንቦት18 ቀን 2005 ዓ.ም
በዶሃ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ
የቆንስላ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች
አጠቃላይ ሁኔታ
የሥራ ቀናት
-
የቆንስላ አገልግሎት ከእሁድ እስከ ሐሙስ ክፍት ነው፣
-
ከ8፡00AM-2፡00PM አገልግሎት ይሰጣል፣
-
ቆንስላ አገልግሎቱ በኢትዮጵያና ቀጣር የሕዝብ በዓላት ቀን አገልግሎት አይሰጥም፣
-
ከኤምባሲ መረጃ ለማግኘት፣
-
Um Guwaifa street No, 804
-
Area Al katifia No, 66 Al-Dafna,
Doha, Qatar በሚገኘው ኤምባሲያችን በአካል በመገኝት ወይም
በስልክ ቁጥር (00974) 40207000 እና
በE-mail ethioembassydoha@gmail.com መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
ወይም በፋክስ ቁጥር 44719588
ፎቶ ግራፍ
-
ለሁሉም አገልግልት የሚቀርቡ ፎቶግራፎች የፓስፖርት መጠን ያላቸው ሆኖ መልኩ ከጀርባ ነጣ ያለ ሁለቱንም ጆሮ የሚያሳይ፣ ከሃይማኖት ምክንያት ውጭ ኮፍያ እና ሌሎች ራስን የሚሽፍኑ ነገሮችን ተደርጎ ያልተነሳ መሆን አለበት፡፡
-
ከፎቶ ጀርባ የባለቤቱን ሙሉ ስም መፃፍ አለበት፣
-
ለፓስፖርትና ለመታወቂያ አገልግሎት የሚውል ፎቶ ከጠቅላላ ቦታ 50 እጅ ፊት መሸፈን አለበት፡፡
I. ፓስፖርት ነክ ጥያቄ መሟላት ያለበት፣
-
በኤምባሲያችን በኩል ፓስፖርቱ አድሰው ጉዞ ለማድረግ አቅደው ከሆነ ከጉዞ ቀን ወይም ከታደሰ ፓስፖርት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ ቢያንስ 45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅቦታል፡፡
-
ፓስፖርት ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደሞ አዲሱን ፓስፖርት ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡ እድሜአቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ከዚህ ቀድሞ ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዲሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከነበረና አሁን ከ14 ዓመትና ከዚያ በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ፓስፖርትዎ ተዘጋጅቶ እስከሚደርስዎ ድረስ መቆየት የማይችሉና በተለያየ አጣዳፊ ምክንያቶች በአስቸኳይ ወደ አገር ቤት መሄድ ከፈለጉ ወደ አገር ቤት መግቢያ የሚያገለግለውን ሊሴ ፓሴ ብቻ (የሊሴ ፓሴ አገልግሎት ክፍያ ከፍለው) ወስደው ከአገር ቤት ፓስፖርት ማመልከት ይችላሉ።
-
የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ ጉዞዎ ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ ከኢሚግሬሽን ፓስፖርትዎን መረከብ ይችላሉ።
-
ኤምባሲው የዶላር አካውንት ያልከፈተ በመሆኑ ለሚንሰጣቸው አገልግሎት የምናስከፍለው በቀጣር ሪያል በካሽ (cash) መሆኑን እንዲታወቅ፣
-
አገልግሎቱ ያለቀ ፓስፖርት ለመቀየር/ለማደስ
-
4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ 6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣
-
ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ዋናው ፓስፖርት ማቅረብ፣
-
ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ገጽ በሁለት ኮፒ ማቅረብ፣
-
በቀጣር መኖርያ / የሥራ ፍቃድ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ፣
-
የአገልግሎት ክፍያ 50 ዶላር ወይም 183.00 ቀጣር ሪያል፣
-
የጣት አሻራ ማቅርብ ለሚጠበቅባችው በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማረጋገጠ ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ፣
-
ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ፣ ቅጽ 2 በሁለት ኮፒ (2 ገጽ) ሞልቶ ማቅረብ፣
2. በጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት ለመቀየር
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. 4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ 6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣
2. ኢትዮጵያዊነትን የሚያስረዱ ሰነዶች በሁለት ኮፒ ማቅረብ/ የቀድሞ ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ገጽ ወይም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ ወይም የቀበሌ መታወቂያ፣
3. በቀጣር መኖርያ / የሥራ ፍቃድ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ፣
4. የአገልግሎት ክፍያ $60.00 ዶላር ወይም 219 ቀጣር ሪይል፣
-
የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማረጋገጠ ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ፣
-
ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ፣ ቅጽ 2 በሁለት ኮፒ (2 ገጽ) እና ቅጽ 3 በአንድ ኮፒ(1 ገጽ) ሞልቶ ማቅረብ፡፡
3. በወላጆቻቸው ፓስፖርት ተለጥፈው ሲጓዙ ለነበሩ ህጻናት ወይም ከዚህ ቀደሞ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ፓስፖርት ያልወሰዱና ለመጀመሪያ ጊዜ ፓስፖርት ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. 4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ 6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣
2. ኢትዮጵያዊነትን የሚያስረዱ ሰነዶች በሁለት ኮፒ ማቅረብ (ከወላጆቻቸው ጋር የተጓዙበትን ፓስፖርት ኮፒ ወይም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ ወይም የቀበሌ መታወቂያ)፣
3. በቀጣር መኖርያ / የሥራ ፍቃድ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ፣
4. የአገልግሎት ክፍያ፡-
-
ለአዋቅ $55.00 ዶላር ወይም 183 ቀጣር ሪያል፣
-
ለህፃናት $25.00 ዶላር ወይም 92 ቀጣር ሪያል፣
5. የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ፣
-
ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ ( 1 ገጽ) ፣ ቅጽ 2 በሁለት ኮፒ (2 ገጽ) እና ቅጽ 3 በአንድ ኮፒ(1 ገጽ) ሞልቶ ማቅረብ፡፡
II. ሊሴ ፓሴ ለማመልከት
-
የአገልግሎት ጊዜውን ያበቃ ፓስፖርትዎ ለመለወጥ ወይም ለማሳደስ በቂ ጊዜ ከሌለዎትና በተለያየ አስቸኳይ ምክንያት ወደ አገር ቤት ለመጓዝ ከፈለጉ ሊሴ ፓሴ መጠየቅ ይችላሉ፡
-
ሊሴ ፓሴው ለአንድ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መግቢያ ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ ሲመለሱ ከኢትዮጵያ ፓስፖርት ማውጣት እንዳለብዎ አይዘንጉ፡፡
-
ፓስፖርትዎ ተዘጋጅቶ እስከሚደርስዎ ድረስ መቆየት የማይችሉና በተለያየ አጣዳፊ ምክንያቶች በአስቸኳይ ወደ አገር ቤት መሄድ ከፈለጉ ወደ አገር ቤት መግቢያ የሚያገለግለውን ሊሴ ፓሴ ብቻ (የሊሴ ፓሴ የአገልግሎት ክፍያ በመክፈል) ወስደው ከአገር ቤት ፓስፖርት ማመልከት ይገባዎታል።
-
የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ ጉዞዎ ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ ከኢሚግሬሽን ፓስፖርትዎን መረከብ ይችላሉ።
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
3 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ 6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣
-
አገልግሎቱ ያበቃውን ፓስፖርት በሁለት ኮፒ ማቅረብ፣
-
ፓስፖርትዎ ከተጠፋ ወይም ከሌሎዎት የትና መቼ እንደወሰዱት የሚገልጽ ማስታወሻ እንዱሁም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ማቅረብ፣
-
በቀጣር መኖርያ / የሥራ ፍቃድ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
-
የአገልግሎት ክፍያ $20.00 ዶላር ወይም 73 ቀጣር ሪይል፣
-
ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ፣ ቅጽ 2 በሁለት ኮፒ (2 ገጽ)
-
የግራና ቀኝ እጅ አመልካች ጣቶች አሻራ ሲሰጥ፣
III. የተለያዩ ሰነዶችን የማረጋገጥ አገልግሎት
-
ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚመጡ ዶክመንቶች ከቀጣር መንግስት የመነጨ ከሆነ (ለምሳሌ - ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣ የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን …) መጀመሪያ ቀጣር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶኩመንቱን ተረጋግጦ ወደ ኤምባሲው መምጣት አለበት፡፡
-
ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደኛ በመላክ/በማምጣት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ
1. በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ከኢትዮጵያ ለመጡ የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. መጀመሪያ ለማረጋገጥ የሚፈለጉ ዶኩመንቶች በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተረጋግጦ መቅረብ አለባቸው፣
2. የጋብቻ፣ የልደት፣ የትምህርት መረጃ… የአገልግሎት ክፍያ መጠን 50.00 ዶለር 183 ቀጣር ሪያል ነው፣
3. ለፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ለማረጋገጥ 52 ዶላር /190 ቀጣር ሪያል ነው፣
4. የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ በማቅረብ ሲፈፅሙ፣
5. የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው የጋብቻ፣ የልደት፣ የትምህርት መረጃ… የአገልግሎት ክፍያ መጠን 78.00 ዶላር (ለፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ለማረጋገጥ 83.00 ዶላር) ክፍያ ይፈፅማሉ፣
6. ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ፣ ቅጽ 3 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ)፣
2. ከቀጣር መንግስት ለተሰጡ የተለያዩ ዶክመንቶችን ለማረጋገጥ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
መጀመሪያ በቀጣር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶክመንቶቹ ተረጋግጦ ወደ ኤምባሲው መምጣት አለበት፡፡
-
የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ በማቅረብ
-
የአገልግሎት ክፍያ መጠን 52.00 ዶለር ክፍያ ሲፈፅሙ፣
-
የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው 68.00 ዶላር ክፍያ ይፈፅሙ፣
-
ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ፣ ቅጽ 3 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ)
IV. የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ አገልግሎት
-
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ከተዘጋጀ በኋላ በኤምባሲያችን ወይም ቆንስላ ክፍላችን ዘንድ ቀርበው ፈርመው መረከብ ይጠበቅቦታል፡፡
-
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርዱ ለ5 አመት የሚያገለግል ይሆናል፡፡ የአገልግሎቱ ዘመኑ ከ1ዓመት በፊት ያበቃ መታወቂያ ካርድ ከያዙ በፈቃድዎ መታወቂያ ካርዱን እንደመለሱ ይቆጠራል፡፡
-
የአገልግሎት ዘመኑ እስካለበት ድረስ መታወቂያ ካርዱን በመያዝዎ ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት ይችላሉ፡፡
-
ከ18 ዓመት በታች ልጆች ካልዎት የልደት ማስረጃውን ከሰጠው አገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መ/ቤት በኩል አረጋግጠው በሁለት ኮፒ በማቅረብ በመታወቂያ ካርዱ ላይ አስመዝግበው ከእርሶ ጋር ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት ይችላሉ፡፡
-
በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ መታወቂያ ካርዱን ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት ሁለት ኮፒ፣
-
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ዋናውና መረጃ ያለበትን ገጽ ሁለት ኮፒ፣
-
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ፣
-
ሶስት (3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣
-
የአገልግሎት ክፍያ 100 ዶላር፣
-
መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት፣
-
በትውልድ ኢትየጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖራቸው ለባለቤታቸው ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት ሁለት ኮፒ፣
-
የጋብቻ የምስክር ወረቀት ከተሰጠበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ሁለት ኮፒ (ጋብቻው ቢያንስ ለሁለት አመት የፀና መሆን ይኖርበታል)፣
-
ሶስት (3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣
-
የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የአመልካች ወይም ባለቤት የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ፣
-
የአገልግሎት ክፍያ 100ዶላር፣
-
መጠየቂያ ቅጽ-2 በሁለት ኮፒ መሙላት፣
3. መታወቂያ ካርዱ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ለሚጠይቁ
-
ያለዎት መታወቂያ ካርድ ማንዋል (ቢጫው) ከሆነ ባሉት ሶስት ገጻች ላይ ታድሶ ሊሠጠዎ ይችላል፡፡ የሚታደሰው ገጽ ከሌለውት ግን የተዘጋጀልዎትን ተለዋጭ መታወቂያ ካርድ ፈርመው መረከብ ይኖርበታል፡፡
-
ያለዎት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪደብል (አዲስ አበባ ከሚገኘው ከዋናው መ/ቤት የሚሰጠው) ከሆነ እዚያው ላይ ማሳደስ ስለማይቻል የተዘጋጀለዎትን ተለዋጭ መታወቂያ ካርድ በአካል ቀርበው መረከብ ይኖርቦታል፡፡
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
የቀድሞ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውንና ኮፒውን ማቅርብ፣
-
የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት ኮፒ፣
-
ሁለት (2) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያ ለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣
-
የአገልግሎት ክፍያ 40 ዶላር፣
-
መጠየቂያ ቅጽ መሙላት፣
4. በጠፋ ወይም በተበላሸ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት ኮፒ፣
2. የቀድሞ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ (የመታወቂያ ኮፒ ከሌለዎት መቼ እና ከየት እንደወሰዱት የሚገልፅ ማስታወሻ አያይዘው ያቅርቡ)፣
3. ሶስት (3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣
4. የአገልግሎት ክፍያ 60ዶላር፣
5. መጠየቂያ ቅጽ መሙላት፣
5. ሲጠቀሙበት የነበረ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለመመለስ ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያውን ማቅረብ፣
2. መታወቂያው በፍላጎትዎ የሚመልሱ ለመሆኑ ማስታወሻ ጽፈውና ፈርመው ማቅረብ፣
3. መጠየቂያ ቅጽ-4 መሙላት፣
V.የውክልና አገልግሎት
-
ዜግነትዎ ኢትያጵያዊ ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካልዎት ኤምባሲው ዘንድ በአካል ቀርበው የውክልና ሰነዱን ኦፊሰሩ ባለበት ፈርመው ማስፈፀም ይኖርበታል፡፡
-
የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው ውክልናውን በአማርኛና በእንግለሊዘኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ በመጀመሪያ በቀጣር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጦ መቅረብ፡፡
1. ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ፣( በተዘጋጀ ቅጽ 7 ላይ በአካል በመገኝት በቆንስላ ሰራተኞች ፊት መፈረም)፣
2. የታደሰ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ፣
3. በቀጣር መኖርያ / የሥራ ፍቃድ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ፣
4. ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ፣ ቅጽ 4 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ሞልቶ ማቅረብ፣
-
ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
2. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
በአማርኛና በእንግሊዘና ጽፈው ያዘጋጅቱን ውክልና በመጀመሪያ በቀጣር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጦ መቅረብ፣
-
የአገልግሎት ክፍያ 83 ዶላር፣
-
ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ፣ ቅጽ 3 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ሞልቶ ማቅረብ፡፡
3. የአትዮጵያዊ ዜግነት ላላቸው
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ ( በተዘጋጀ ቅጽ 6 ላይ በአካል በመገኝት በቆንስላ ሰራተኞች ፊት መፈረም)፣
-
የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ፣
-
በቀጣር መኖርያ / የሥራ ፍቃድ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ፣
-
ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
-
የአገልግሎት ክፍያ 52 ዶላር፣
-
ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ፣ ቅጽ 3 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ሞልቶ ማቅረብ፡፡
VI. ከወንጀል ነፃ መረጃ
-
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
2 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣
-
የታደሰ ፓስፖርት ወይም የጋብቻ / የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወይም ሌሎች በኢትዮጵያ መንግስት የተሰጡና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ፣
-
የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ዋናውን ማቅረብ፣
-
የአገልግሎት ክፍያ $52 ዶላር
-
ቅጽ 1 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ) ፣ ቅጽ 3 በአንድ ኮፒ (1 ገጽ)
ወደ አገር ቤት ሲልኩ
-
ኦርጅናል የጣት አሻራ ዶክመንት ወደ ፌደራል ፖሊስ ፎሬንሲክ ምርመራ ክፍል በአካል፣ በተወካይ ወይም በፖ.ሣ.ቁ. 80358 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በማለት
-
የጣት አሻራ ዶክመንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ (ኢትዮጵያ)፣
-
ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
-
ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ኮፒ መላክ/ማቅረብ
-
ከፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መረጃ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኤምባሲው በማረጋገጥ አገልግሎት ላይ ማዋል፣
-
አገር ቤት አገልግሎቱን በአካል ወይም በተወካይ ማግኘት ይቻላል፡፡
-