top of page

ዜና

የአፍሪካ እድገት ማሳያዋ ኢትዮጵያ ነች፡- ባራክ ኦባማ

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 16/ 2006

በመግለጫቸው ላይ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ ወደፊት እየተሻገረች መሆኗን በማንሳት በዚህ ሽግግር ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

ራስን ለማልማት የሰው ሀይል አቅምን ማሳደግ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም በዚህም ሂደት ዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ፕሮግራሞች ድጋፏን በማድረግ ጤነኛ አምራች ሀይል እንድናፈራ አግዛናለች ነው ያሉት።

በፓወር አፍሪካ ፕሮግራም በኩል ኢትዮጵያ በሀይል ለማት ዘርፍ የግል ዘርፍን እንድታሳትፍ አሜሪካ ላደረገችው ድጋፍም አቶ ሀይለማርያም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፈን እያደረገች ያለችውን ጥረት አንስተው፥ ይህ ስራዋን ከአፍሪካ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ብሎ ለዓለም ሰላም የምታደርገውን ድጋፍ ማሳደግ ትፈልጋለች ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በበኩላቸው በቅርቡ በአፍሪካ አሜሪካ ጉባኤ ላይ በአህጉሪቱ እየታየ ያለውን ብሩህ ነገር እና ለውጥ ለማሳየት ከኢትዮጵያ የተሻለ ምሳሌ የለም ሲሉ ንግግራቸውን ጀምረዋል፤ ኢትዮጵያ በዓለም በፍጥነት እያደጉ ካሉ የዓለም አገራት መካከል አንዷ መሆኗን በማንሳት።

ዶ/ር ቴድሮስ ከዩናይትድ ኪንግደም የውጪና የጋራ ብልፅግና አገራት ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14/2007

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14/2007 (ዋኢማ) - የኢፌድሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ከዩናይትድ ኪንግደም የውጪና የጋራ ብልፅግና አገራት ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ ፍሊፕ ሀሙድ ጋር ተወያዩ።
ዶክተር ቴድሮስ በአሜሪካ ዋሽንግተን ከተካሄደው የልማት ፎረም ጎን ለጎን ነው ከዋና ፀሃፊው ጋር የተወያዩት።

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮች ግንኙነት ፣አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በዚሁ ወቅት ዋና ፀሀፊው እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እየተወጣች ያለውን አርአያነት ያለው ሚና አድንቀዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን የተፈጠረውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ እና በድርድር ብቻ  እንዲፈታ ለማስቻል የተጫወተችው ያደራዳሪነት ሚናም ያስመሰግናታል ብለዋል።

ዶክተር ቴድሮስ በበኩላቸው፥ የደብብ ሱዳን መሪዎች ድርድር በኢትዮያዋ ባህር ዳር መቀጠሉን አውስተው፥ በአገሪቱ ያለውን ቀውስ ለመፍታት ተቀናቃኞቹ የገቡትን ቃል 

ጠ/ሚ ሀይለማርያም የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ዕቅድን በኒውዮርክ ለተመድ ጉባኤተኛ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15/ 2007

ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2025 ላይ አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ ያስቀመጠቸውን የረዥም ጊዜ ዕቅድ በኒውዮርኩ እየተካሄደ ባለው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ  ጉባኤ ላይ አቅርቡ።

የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚን መሰረት በማድረግ የበካይ ጋዝ ልቀትን ዜሮ ያደረሰች መካከለኛ ገቢ ያላት አገር ለመፍጠርም ኢትዮጵያ የተለመደውንና ለአከባቢ ጥበቃ ትኩረት የማይሰጠውን የኢኮኖሚ ግንባታ አካሄድ እንደማትከተል ነው በንግግራቸው የጠቆሙት።

አገራት በኢኮኖሚ ሲያድጉ ወደ ከባቢ ዓየር የሚለቁት የበካይ ጋዝ መጠን ሲጨመር መምጣቱን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ በተቃራኒው አንስተኛ ወይም ዜሮ የበካይ ጋዝ ልቀትን ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም የታዳሽ ሃይልን በአማራጭ የሀይል ምንጭነት በመጠቀም፤ የባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ  ዕድገት ማስመዝገብ እንደሚቻል አሳይታለችም ነው ያሉት።

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት ወር የመጀመሪያው ሰኞ እንዲከበር ተወሰነ

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 9/2007

በአገር አቀፍ ደረጃ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት ወር የመጀመሪያው ሰኞ እንዲከበር መደረጉን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበር አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ምክር ቤቱ በ2006 ዓ.ም.በ19ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ባደረገው ማሻሻያ በፊት ከሚከበርበት መስከረም ወደ ጥቅምት ወር የመጀመሪያው ሰኞ እንዲከበር ወስኗል፡

እለቱ የተቀየረበት ዋና ምክንያት የመስከረም ወር  የምክር ቤቱ አባላት የእረፍት ጊዜ ላይ የሚሆኑበት ወቅት በመሆኑ ምክር ቤቱን ሙሉ በሙሉ ማሳተፍ ባለመቻሉ ነው ብለዋል

አፈ ጉባዔው እንዳሉት ''የሰንደቅ ዓላማ ቀን እንደ ሌሎች በዓላት ስራ ተዘግቶ የሚከበር ሳይሆን በስራ የሚከበር በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ስራው ላይ ሆኖ እንዲያከብር በተለይ የመጪው አገር ተረካቢ ትውልድ ሙሉ በሙሉ ወደ ትምህርት ቤት ከተመለሰ በኋላ መሆን ስላለበት ነው'' ብለዋል

Please reload

bottom of page